Tuesday, June 18, 2013

ኢትዮጵያ የአስዋንን ግድብ በሚሳይል እንድታፈነዳ ሀሳብ ቀረበ ::


 
የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የሕዳሴውን ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ፣ አንድ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ኤክስፐርት የግብፅ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ 1 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ በቂ ነው ሲሉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።

ኤክስፐርቱ እንደገለፁት ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግንባታ ግድብ በጦር መሣሪያ ለመምታት ካስቀመጠቻቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን በመጠቆም ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመታ ለኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በአፀፋው የአስዋን ግድብን እንዲመታ ሕጋዊ ፍቃድ መስጠቷን ልታውቅ ይገባል ብለዋል።

አያይዘውም፤ ግብፅ በወታደራዊ እቅዷ ከገፋችበት በኢትዮጵያ በኩል አማራጭ መንገዶችን መመልከት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻ አድርገህ ላቲቲውዱን 14.3000 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 36.6167 ዲግሪ ብትወስደው እንዲሁም አስዋን የሚገኝበት ላቲቲውድ 23.9706 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 32.8779 ዲግሪን አቀናጅተህ ብታሰላው በአየር ላይ ያለው ርቀት 1100 እስከ 1500 ኪሎ ሜትር የአየር ርቀት ነው ያለው። በዚህ ውጤት መነሻ የኢትዮጵያ መንግስት 1500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ የስከድ ሚሳኤሎችን መታጠቅ ብቻ በግብፅ አሰዋን ግድብ ተመጣጣኝ ሃይል ሊፈጥር ይችላል።”  ብለዋል።

ወታደራዊ የአየር ርቀቱን ለመለካት የተሄደበትን አሰራር ቢያብራሩት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ ይህ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። http://www.movable-type.co.uk/scripts/latlong-gridref.html በሚለው ድረ ገጽ ዲግሪውን በመጠቀም ማስላት ይቻላል። ቁም ነገሩ ግን ወታደራዊ አማራጭ ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ አያደርግም። ብቸኛው አማራጭ በዲፕሎማሲ ደረጃ ለመፍታት መሞከር ነው ሲሉ ኤክስፐርቱ አሳስበዋል
በአሁን ሰዓት በዓለማችን ላይ 1 500 ኪሎ ሜትር እስከ 15 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል የታጠቁ ሀገሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲአረቢያ እና አሜሪካ ይገኙበታል:: (ምንጭ  ሰንደቅ  ጋዜጣ)  

Sunday, June 16, 2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ባደረገው ግጥሚያ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸነፈ ::


 
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ባደረገው ግጥሚያ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸነፈ :: ኢትዮጵያም 2014 የብራዚል ያለም ዋንጫ ውድድር ስሟ ካስሩ አገሮች ተርታ ገባ ::
የዋልያዎቹን ጨዋታ ለማየት ስፖርት አፍቃሪው ወደ አዲስ አበባ ስታዲዮም መግባት የጀመረው እሁድ ሳይሆን ከቅዳሜ ምሽት ጀመሮ ነበር :: በመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ሰአት የደቡብ አፍሪካው ቡድን በጨዋታ በልጦ የታየበት ሲሆን 33ተኛው ደቂቃ ላይ 17 ለብሶ የሚጫወተው የደቡቡ አፍሪካው አጥቂ ፓርከር ለቡድኑ የመጀመሪያዋን ጎል ማስቆጠር ችሏል :: ይሁን እንጂ ዋልያዎቹ ተስፋ ባለመቁረጥ ባደረጉት የመልስ ማጥቃት 40ኛው ደቂቃ ላይ ከደደቢት የተመረጠው ጌታነህ ከበደ አስተካክሎ የተሰጠውን ኴስ አመቻችቶ በመምታት ለውጤት አብቅቶታታል
::
በሁለተኛው አጋማሽ ላይ የኢትዮጵያ ቡድን ያገኛትን ቅጣት ምት የደቡብ አፍሪካው ተጫዋች ለማውጣት በቴስታ ሲሞክር በራሱ ጎል ላይ ዶሏታል :: በዚህ ጨዋታ ላይ አጫዋቾች የነበሩት የመኅል ዳኞችና የመስመር ዳኞች በሙሉ ከግብጽ የነበሩ ሲሆን ሰሞኑን ባባይ ዙሪያ በኢትዮጵያና በግብጽ በተነሳው ውዝግብ ሳቢያ ዳኞቹ ሊያደሉ ይችላሉ የሚል ፍርሀት በመላው የስፖርት ቤተሰቦች ላይ አድሮ ነበር :: ይሁን እንጂ ጨዋታው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ዳኞቹ ፍጹም አድልዎ በሌለበት ሁኔታ ጨዋታውን በመምራታቻው የቡዙዎችን አድናቆትና አክብሮት አግኝተዋል :: የስፖርት ተመልካቹም ሙሉውን 90 ደቂቃ ድጋፉን ለዋልያዎቹ ቢያደርግም "" ማንዴላን እናፈቅረዋለን "" የሚል ትልቅ መፈክር በመያዝ ለደቡብ አፍሪካ ስፖርተኞች ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል :: ( የኢትዮጵያ በዚህ ሳምንት ዋና አዘጋጅ )

Total Pageviews

 
Design by Free WordPress Themes | Bloggerized by Lasantha - Premium Blogger Themes | Justin Bieber, Gold Price in India