በመጀመሪያ መምህር ነበረ፤ በኋላ የረጅም ዘመን የራዲዮ ጋዜጠኛ! ድሮ በብሥራተ ወንጌል ራዲዮ ጣቢያ ዓለምን እንይ! የሚል ተወዳጅ ዝግጅት ነበረው።በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንም፣ ህዝብና ጤናው የተሰኘ ዝግጅት ያቀርብ ነበር። በዶቸ ቨለ ይበልጥ የሚታወቀው በእስፖርት ፕሮግራም አዘጋጅነቱ ነው። ከ 4 ዓመት ከመፈንቅ ገደማ በፊት ጡረታ እስከወጣበት ጊዜ ድረስም በተጨማሪ የአማርኛው ክፍል ኀላፊ ነበረ። አማኑኤል በረከት ሥራውን እጅግ የሚወድ፤ በሥርዓት የታነፀ፣ ከሰዎች ጋር በጣም ጥሩ የመግባባት ችሎታ የነበረው፤ በመቻቻል የሚያምን፣ ሰዎችን ለማስደሰት የሚንሠፈሰፍ፤ እጅግ ሰላማዊ፤ ትሁትና ለጋስ ሰው ነበረ።
በዛሬው ዕለት ቦን አቅራቢያ በምትገኘው «ባድ ሆኔፍ» በተባለችው ከተማ፤ ከዩናይትድ እስቴትስ የመጡት እህቱ፤ ወንድሞቹ፤ በጀርመን የሚገኙት ባለቤቱ፤ ልጁ፣ የልጅ ልጆችና ቤተሰብ፣ ዘመዶች፣ እንዲሁም ከቦን ኮሎኝና ከሌሎችም የጀርመን ከተሞች ፣ በዛ ያሉ የረጅም ጊዜ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹና የሥራ ባልደረቦቹ በተገኙበት የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል። ከDW የአማርኛው ክፍል ሌላ፤ የተለያየ ቋንቋ ክፍል ሠራተኞችም የተገኙ ሲሆን፤ የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት ለሥርጭታችን በሚያመች መልኩ መሳይ መኮንን ተከታትሎታል። ምንጭ (ዶቸ ቨለ ድህረ ገጽ)
ለጥንክሩ እቺን ይጫኑ::














Siye Abraha, Unity for Democracy and Justice Party (UDJ) public relations officer and former Tigray Peoples’ Liberation Front (TPLF) leader and Ethiopian Defense Minister, acquired a scholarship to study at Harvard University in Boston, U.S.A, the party disclosed.Siye, who joined the UDJ a year and a half ago, was honored at a farewell festivity the party held at the Addis View Hotel last Sunday, May 15. “He is a highly disciplined individual with insight in economic and political matters,” Negassu Gidada, president of the party said at the event.Siye, on his part, pay tribute to his party saying it is one that will “reach to great heights, and with a lot of potential.” He further vowed to serve UDJ and the Ethiopian people upon his return with the knowledge he acquires at Harvard.Harvard University awards this scholarship to senior government officials who have been in office for at least ten years, and are proven competent in their educational background. Siye will stay in school for one year for this Master of Arts program in Government, Policy and Leadership training. Source (Reporter)
















